ፍራሽ ከመግዛታችን በፊት……..

በፈለግነው ጊዜ እንደምርጫችን ፍራሽ መለወጣችን እንደተጠበቀ ሆኖ የኢንዱስትሪው ባለሙያዎች ከ5-7 ዓመት ጊዜ ውስጥ ፍራሻችንን እንድንለውጥ ይመክራሉ፤ ከጊዜ ብዛት አቧራ፣ የሞቱ የቆዳችን ሴሎች እንዲሁም ላብ ተጨምሮበት ለተለያ ባክቴሪያዎችና ፈንገስ መራቢያ የተመቻቸ ያደርገዋል፡፡ ልንገዛ ስንሄድ የአልጋችንን ልኬት እንዲሁም ፍራሻችን በምን ያህል ውፍረት እንደምንፈልግ ማወቅ አለብን ከአልጋችን ቅርፅና ዲዛይን ጋር በሚሄድ መልኩ ማለት ነው፡፡
እስኪ እነዚህን በጣም የተለመዱ የአልጋ ልኬቶችን እንመልከት ፍራሽ ልንገዛ ሄደን የሽያጭ ወኪሎቹ የሚዘረዝሩልንን የፍራሽ ዓይነቶች በተሻለ እንድንረዳቸው ለአጠቃላይ ግንዛቤ ያህል የስፕሪንግ እና ፎም ፍራሽ ዓይነቶችን ብቻ እንመልከት

ስፕሪንግ(Spring)

ከ1990ዎቹ ጀምሮ የነበረ ሲሆን ገበያ ላይ በጣም የሚታወቅ አይነት ነው፡፡ ከብረት የተሰሩ ስፕሪንጎች (ጥቅልሎች) የተሰራ ነው፡፡ የስፕሪንጎቹ ቅርፅ፣ መጠንና ብዛት አንዱ ከሌላው ሊለያይ ይችላል፡፡በአጠቃላይ ብዙ ስፕሪንግ ያለው ፍራሽ አንዱ የጥራት እና የተሻለ ምቾት መገለጫ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል፡፡
በጣም በብዛት የሚገኝ የተለመደ የሚያነጥር ደግፎ የሚይዝ ሲሆን ለማንቀሳቀስ ቀላል ነው ስንገላበጥ ወይም ከእንቅልፋችን ስንነሳ አብሮን የተኛውን ሰው የመበጥበበጥ እድል አለው እያረጀ ሲመጣ ስፕሪንጎቹ ድምፅ ማውጣት ይጀምራሉ፡፡

foam mattress

ፎም(Foam)

እቅፍ የሚያደርግ ምቾትና ልስላሴ ያለው ሲሆን ፍራሻችን ውስጥ ስምጥ ብልን ለመተኛት ተመራጭ ነው የሰውነታችን ክፍል ያረፈበት ቦታ ሰርጎድ ብሎ ይቀርና ተመልሶ ቦታውን ይይዛል በጎን መተኛት ለምናዘወትር ሰዎች እንዲሁም የወገብ ችግር ላለባቸው ሰዎች ይመከራል፡፡
ይህ ፎም ክብደታችንን ለመሸከም ጥቅጥቅ ተደርጎ ስለሚሰራ በቂ የአየር ዝውውር ስለማይኖረው በውስጡ ሙቀት አምቆ ይይዛል፡፡

Call to buy

Main Menu